የአሜሪካ ምርጥ ዜጋና አዲስ የለቀቁት ፊልም

ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም ዛሬ 96 አመት ሞላቸው።የአሜሪካ ህሊና በመባል የሚታወቁትና የሃገሪቱን የምርጥ ዜጋ ኒሻን የተሸለሙት ወንጌላዊው በግምባር ለ200 መቶ ሚሊዮን በሚዲያ ደግሞ ከ1ቢሊዮን ህዝብ በላይ ወንጌል በመስበክ በአለም ታሪክ የመጀመርያው ለመሆን በቅተዋል።።በቀዳማዊ ሃይለ ስላሴ በጎ ፈቃድ በአዲስ አበባ ስቴዲየም ሰብከዋል።በወንጌላዊ ግራሃም ልዩ ግብዣ ንጉሱ በአለም አቀፍ የወንጌላውያን ስብሰባ ላይ የክብር እንግዳ በመሆን

ንግግር አድርገዋል።ወንጌላዊ ቢሊ ግራሃም በአለም መንግስታትና በተለያዩ ሃይማኖቶች መሪዎች የሚከበሩ የፍቅር ሰው ሲሆኑ በኦርቶዶክስና በካቶሊክ አብያተ ክርስቲያናት በመጋበዝ ወንጌል ሰብከዋል።
“የፕሬዚደንቶች ፓስተር” በመባል ሲታወቁ ከሁለተኛው የአለም ጦርነት ወዲህ ባራክ ኦባማን ጨምሮ ለሁሉም የአሜሪካ መሪዎች ጸልየዋል፤የግል ወዳጅም ነበሩ። ዘረኝነትንና ኮሚኒዝምን በአደባባይ በመቃወም ይታወቃሉ።
“ከማንም የተሻልኩ ሳልሆን እግዚአብሔር በኔ ለምን ሰራ? አይገባኝም”ይላሉ ትሁቱ ግራሃም።
በዛሬው የልደት በአላቸው አዲስ የተለቀቀውን HEAVEN የተባለውን ፊልማቸውን እጋብዛችኋለሁ።
http://www.youtube.com/watch?v=Y6twEXynopo
HAPPY BIRTHDAY,BILLY GRAHAM!

Billy HS talkBilly Graham Standing With Russian Orthodox Clergy

bg&hsBilly Graham

Advertisements